1. የማትነኛ/ኔብዩላይዘር ቱቦዎች
2. የማትነኛ/ኔብዩላይዘር የአፍ ጫፍ
3. የማትነኛ/ኔብዩላይዘር እጀታ
4. የ ማትነኛ/ኔብዩላይዘር መያዣ
5. የ ኮረንቲ ማብሪያ/ማጥፊያ
የአጠቃቀም መመሪያ
InnoSpire Elegance
አስፈላጊ መመሪያ፦ ይህንን መሣሪያ ከመጠቀምዎ በፊት ይህንን መመሪያ በጥሞና አንብቡ። ስለ መሣሪያው ችግር ቢያጋጥምዎት
ወይም ጥያቄ ቢኖርዎት እባክዎን የሕክምና አገልግሎት ሰጪዎን ወይም የ Philips Respironics የደንበኞች ማስተናገጃን በስልክ
ቁጥር +1 724 387 4000 ይገናኙ።
አጠቃላይ መረጃ
መሆን ያለበት አጠቃቀም፦ ይህ መሣሪያ የተሠራው ለሕክምና የሚሆን የታመቀ አየር ለማቅረብ ነው። አጠቃቀሙም
በታመቀ አየር ትነት አማካይነት ለማከሚያ እንዲሆን ማናፈሻ ነገሮችን እንዲያስገኝ ነው፡፡ ጥቅሙም ለሕጻናትና ላዋቂዎች/
ለትልቆች ሕክምና እንዲያገለግል ነው፡፡
ማስጠቀቂያዎች
1
ይህ መሣሪያ በመንፊያ የሚረጭ ሕክምና ለመስጠት የሚጠቅም በማመቅ የሚያተን /ክፕምፕሬሰር ኔብዩላይዘር / ዘዴ
የሚሠራ ብልሃት ስለሆነ በዚህ መመሪያ ውስጥ በተገለጸው መሠረት ይጠቀሙበት። ሐኪመዎ የሰጥዎትን መመሪያም
ይከተሉ። ይህንን መሣሪያ ለሌላ ነገር ማዋል አላግባብ ሲሆን አደገኛም ሊሆን ይችላል። ያለአግባብ፣ ትክክል ባልሆነ
መንገድ ወይም በማይሆን መንገድ ተጠቅመውበት ጉዳት ቢደርስ ወይም ከደህንነት ደንቦች ጋር አብረው የማይሄዱ
የኮረንቲ ሶኬቶች ውስጥ ቢሰኩት አምራቹ አካል ተጠያቂ ሊሆን አይችልም።
• ድ ንገት የትነት መሣሪያዎን /ኔብዩላይዘርዎትን መጠቀም የማይችሉበት ሁኔታ ቢፈጠር (ለምሳሌ መብራት ቢጠፋ
ወይም በሆነ ምክንያት አማቂው መሣሪያ/ኮምፕሬሰርዎት አልሠራ ቢል)፡ሌላ ለመተንፈሻ የሚያገለልግ የድንገተኛ
መሣሪያ ቢኖርዎት ጥሩ ነው (ለምሳሌ MDI (እየመዘነ የሚሰጥ መተንፈሻ) ወይም በባትሪ የሚሠራ ኮምፕሬሰር)።
• መ ሣሪያው ከጥቅም ውጪ ሆኖ ቆይቶ ከነበረ፣ እንደገና ከመጠቀምዎ በፊት መደበኛ የአሠራር ሁኔታ ላይ እስከሚመለስ
ድረስ ይጠብቁ።
• ም ንም ዓይነት ፈሳሽ ከውጭውም ላይ ሆነ ከውስጡ ፈሶበት ከነበረ እንደገና ከመጠቀምዎ በፊት እስከሚደርቅ
ይጠብቁ።
2
ይህንን መመሪያ ለወደፊት ይጠቀሙበት ዘንድ ያስቀምጡት።
3
መሣሪያውን ከቆሻሻ፣ ከአቧራ፣ ከእንስሳ ጸጉር፣ ወዘተ. የነጻ ጽዱ አካባቢ ውስጥ ይጠቀሙበት።
4
መ ሣሪያውን በእሳት ሊያያዙ ከሚችሉ ነገሮች አካባቢ ወይም አየር፣ ኦክሲጅን ወይም ናይትረስ ኦክሳይድ ሲያገኝ ሊነድ
ከሚችል ነገር አካባቢ አይጠቀሙ።
5
ይህንን መሣሪያ መለዋወጥ አይፈቀድም።
6
ይህ መሣሪያ ጥቅም ላይ በሚውልበት ጊዜ ሲነኩት ሞቅ ማለቱ ትክክል ነው።
10
6. የማመቂያ/ኮምፕሬሰር ቀዳዳዎች
7. አ የር ማጣሪያ
8. የ ማመቂያ/ኮምፕሬሰር አየር መውጫ
9. የአየር ማስገቢያ ማጣሪያ
7
ኮምፕሬሰሩን ከሌላ ዕቃ ጋር አይደራርቡት።
8
ኤሌክትሮማግኔቲክ መረጃ፦ እንደ ሞባይል ስልክ፣ ፔጀር፣ ወዘተ. የመሳሰሉ ተንቀሳቃሽ እና RFየመገናኛ መሣሪያዎች
በኤሌክትሪክ የሚሠሩ የሕክምና ዕቃዎችን ከሥራ ሊያቋርጡ ይችላሉ። ስለዚህ ኮምፕሬሰርዎ እንዳይቋረጥ ከእንደነዚህ
ዓይነት መሣሪያዎች ማራቅ አለብዎት። ይህ መሣሪያ ስለ ኤሌክትሮማግኔቲክ ብቃቱ (EMC) የ IEC60601-1-2
ደረጃን ያሟላል። የ EMC መረጃ ቅጾችን ለማግኘት Philips Respironics ደንበኛ ማስተናገጃ ስልቅ ቁጥር
+1 724 387 4000 ዘንድ መደወል ይቻላል።
9
መ ሥራት ቢያቆም ወይም ብልሽት ቢያጋጥም "ችግር መፍቻ" የሚለውን ክፍል ያንብቡ። የኮምፕሬሰር መያዣ ቤቱ
አገልግሎት የሚገኝበት ስላልሆነ እንዳይከፍቱት።
10
በ ዋና የመተኪያ ዕቃዎች (ለምሳሌ አየር ማጣሪያ) ካልተጠቀሙ መሣሪያው በትክክል ላይሠራ ይችላል።
11
ኮረንቲ እንዳይይዝዎት፣ ዕቃዎን አይበታትኑ።
12
13
ይ ህንን መሣሪያ ያለ ማጣሪያው አይጠቀሙበት።
14
በ ማንኛውም በኤሌክትሪክ የሚሠራ መሣሪያ ሲጠቀሙ ሁልጊዜ የተወሰኑ የደህንነት ደንቦች መከተል ያስፈልጋል፣
የሚከተሉትን ጨምሮ፡
• አምራቹ ያቀረባቸውን ዋነኛ ዕቃዎችና መለዋወጫ ክፍሎች ብቻ ይጠቀሙ፣
• መሣሪያው ውሃ የማያስገባ መከላከያ ስለሌለው ውሃ ውስጥ መቼም ቢሆን እንዳይነክሩት፣
• እጆችዎ እርጥብ ሆነው መቼም ቢሆን መሣሪያውን እንዳይነኩ፣
• መሣሪያውን ከቤት ውጭ እንዳይተውት፣
• ሲያሠሩት የረጋና ቀጥ ያለ አግድም የሆነ ቦታ ላይ ያስቀምጡት፣
• አየር ማስወጫ ቀዳዳዎቹን የጋረደ ነገር አለመኖሩን ያረጋግጡ፣
• ልጆች ወይም የአካል ጉዳት ያለባቸው ግለሰቦች በግላቸው ያለሰው መሣሪያውን እንዲጠቀሙት አይፍቀዱ፣
• መሣሪያውን እንዳይሠራ ለማጥፋት ገመዱን በቀጥታ ከሶኬቱ አይንቀሉ፣
• በኮረነቲ አየር ማቀዝቀዣ አይጠቀሙ፣
• መሣሪያው ስንጥቅ ካለው ወይም የተጎዳ ከሆነ አይጠቀሙበት።
15
መ ሣሪያውን ሶኬት ውስጥ ከመሰካታችሁ በፊት መሣሪያው ታች ላይ የሚገኘው ደረጃ መስጫ ምልክት ላይ የሚታየው
የኤሌክትሪክ ልክ/ማርክ ከዋና ቮልቴጃችሁ እና ፍሪክዌንሲ ጋር መጣጣሙን ያረጋግጡ።
16
ነጠላም ሆነ ብዙ አዳፕተር እና/ወይም ማራዘሚያ ገመድ አይጠቀሙ።
17
መ ሣሪያውን በማይጠቀሙበት ወቅት እንደተሰካ አይተውት። በማይጠቀሙበት ጊዜ መሣሪያውን ከግድግዳ ሶኬት ነቅለው
ያስቀምጡት።
18
መ ሣሪያውን መጀመሪያ ለመሰካካት የአምራቹን መመሪያ ይከተሉ። ያላግባብ ተሰካክቶ ለተፈጠረ ጉዳት አምራቹ ተጠያቂ
ሊሆን አይችልም።
19
ተጠቃሚው የኤሌክትሪክ ገመዱን መተካት አይችልም። የኤሌክትሪክ ገመዱ ቢጎዳ የ Philips Respironics ደንበኛ
ማስተናገጃ ጋር ደውለው መተኪያ ይጠይቁ (መጠገን አይቻልም)።
20
መሣሪያውን ከማጽዳትዎ በፊት ወይም ማጣሪያውን ከመተካትዎ በፊት ገመዱን ከሶኬቱ ይንቀሉት።
21
አ ንዳንዶቹ ክፍሎች በጣም ትናንሽ ሲሆኑ ልጆች ሊውጧቸው ይችላሉ። ልጆች ያለጠባቂ መሣሪያው ዘንድ እንዲጠጉ
አይፍቀዱ።
SLOVENŠČINA
ENGLISH
11